"በሄወታችን ከልብ የምንወደውን ስራ ለመስራት መታገል አልበን፣ ለምን? በምንወደው ስራ ብንደክም ፡ በስራው ብዛት ብንጠመድ እንኩዋን ስራው ስራነቱ ቀርቶ መዝናኛችን ነው የሚሆነው። "
ሰለሞን ለማ ( ሶልጂት )
ሰለሞን እንደሚለው "አሁን የኔ ጊዜ ነው እዚ ያደረሰኝን ህዝብረተሰብ የማግዝበት ሰርከስ ናዝሬት በነበርኮበት በርካታ አመታትም እያጨበጨበ የሰርከስ ትርዒት ሳቀርብ በርታ እያለ ላጠነከረኝ ህዝብ እንዴሁም ከ 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በነጻ አስተምራ ቻይና ድረስ ልካ Professional ላረገችኝ ሃገሬ ብድሬን የምመልስበት ውቅት ነው።" ለዜህም ይመስላል በህገር አቀፍ ደረጃ 5 የጥበብ ማእከላት ለመክፈት በአዳማ ከተማ አንድ ብሎ የጀመረው። መቀመጫው አዲስ አበባ የሚሆነው ይህ ተቆዋም SunEko ይባላል ይህም በመጀመርያው መርሃ ግብር ለ150 ህጻናት እና ወጣቶችን የሚያቅፍ ይሆናል የዚህ ተቃም አላማም የተለያዮ የሰርከስ ፣ የሞዚቃ ፥ የስእል ፣ የጅምላስቴክ ወዘተን በመጠቀም ህጻናት እና ወጣቶችን በትምህርታቸው የበለጠ ከማጠንከር በተጨማሬ ተስጦዋቸውን በዚ ተቆዋም ፈልገው እንዲያገኞ ማገዝ ነው።
ስለ ሰለሞን ፣ ስለSunEko ፕሮጀክት ወይም አዲስ ስለከፈተው የበይነመረብ (internet) ሬዲው ከታች የተቀመጡትን ቁልፍ በመጫን ሬዲውኖንም መከታተል ፣ የሰለሞንንም አስቂኝ ፣ አዝናኝ ፣ አስተማሬ ቪዲውችን እና ምስሎችን መመልከት ይችላሉ። ፕሮጀክቶንም በሃሳብ ፣ በቁሳቁስ ፣ በገንዘብ ለመደገፍ ከፍለጎ እሱን በቀጥታ ማነጋገር በቀላሎ ማግኝት ይችላሎ። በማህበራዊ መገናኛ ዘዲዎች ምላሹ ፈጣን ነው።