top of page

NEW ቀንዲል Magazine  Click here 👉

ቀንዲል Magazine - Solomon Solgit 01

 ሰለሞን ሶልጅት ማን ነው ?

    ሰለሞን ሶልጅት ሰርከስ በኢትዮጵያ ካፈራቸው በርካታ ኢንተርናሽናል የሰርከስ አርቴስቶች አንዱ ነው። በበርካታ የአውሮፓ ሚድያዎች እና ድህረ ገጾች ላይ ሰለሞን ሶልጅት በመባል የሚታወቀው ሰለሞን ለማ ገብረጻዲቅ ትውልዱ በአዲስ አበባ ሲሆን እድገቱ ደሞ በናዝሬት አዳማ ከተማ ነው። በሰርከስ ናዝሬት ውስጥ ከ11 አመታት በላይ ባለው ተሰጥው ሲያገለግል የቆየ ሲሁን  ከኢትይዮጵያ ከተመረጦ ጥቄት አርቲስቶች ጋር በመሁንምም በቻይና "China wuqiao international college" ተመርቋል። እንዲሁም ከ6 ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን "አቢሲኒያ Jugglers" የተባለ ቡድን በመመስረት በተለያዮ የአለም ሃገራት ፣ በኤዥያ ፣ በአውሮፓ እና በአሜሬካ እጅግ በርካታ በሆኑ ከተሞች ላይ የኢትዮጵያን ባህል እና ስም ሲያስጠሩ ቆየተዋል።

 

    ሰለሞን ሶልጅት የብዙ ተሰጥዉ ባለበት ነው ለምሳሊም :- Break ዳንስ ይደንሳል የBreak ዳንስ ስልጠና በሚኖርበት ጀርመን ከተማ  የሰጣል ፣ በገመድ ላይ ቅልብልቦሽ ሲጫወት ፡ በገመድ ላይ የባለ አንድ እግር  ጎማ ሳይክል ሲነዳ ፡ ከዛም አልፍዉ በዛው በቀጭንዋ ገመድ ላይ በመንሰላል ወደላይ ሲወጣ በሰለሞን ትርዒት የማይደነቅ የለም። 7 ድብልብል ኩዋሶችን በአንድ ጊዜ እየወረወረ ሲያቅለበልብ አንዱ ከአንዱ ኳስ አለመጋጨታቸው ይደንቃል።

   

 ስለ ሙዚቃ ካወራንም ሰለሞን አለበት። ዘመናዊም ሁነ ባህላዊ ከበሮን አቀላጥፎ ይጫወታል፣ ኪቦርድ ፣ ጊታር... ብቻ ሰለሞን የባለ ብዙ ተሰጥዉ ባለበት ነው። በአፍሬካ ሞዚቃ መስክ በመካከለኛው እና በምእራም አፍሬካ ሃገራት የሚታወቀዉን "African Djembe Drum" በሆላን በአውስትሬያ አንዲሁም መጀርመን ለበርካታ ህጻናት እና ወጣቶች ላለፎት 4 አመታት በበረካታ ትምህርት ቤቶች እና የወጣቶች ማእከል ስልጠና ሲሰጥ ቆይትዋል።

 

ሰለሞን እንደሚለው "አሁን የኔ ጊዜ ነው እዚ ያደረሰኝን ህዝብረተሰብ የማግዝበት ሰርከስ ናዝሬት በነበርኮበት በርካታ አመታትም እያጨበጨበ የሰርከስ ትርዒት ሳቀርብ በርታ እያለ ላጠነከረኝ ህዝብ እንዴሁም ከ 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በነጻ አስተምራ ቻይና ድረስ ልካ Professional ላረገችኝ ሃገሬ ብድሬን የምመልስበት ውቅት ነው።"  ለዜህም ይመስላል በህገር አቀፍ ደረጃ 5 የጥበብ ማእከላት ለመክፈት በአዳማ ከተማ አንድ ብሎ የጀመረው። መቀመጫው አዲስ አበባ የሚሆነው ይህ ተቆዋም SunEko ይባላል ይህም በመጀመርያው መርሃ ግብር ለ150 ህጻናት እና ወጣቶችን የሚያቅፍ ይሆናል የዚህ ተቃም አላማም የተለያዮ የሰርከስ ፣ የሞዚቃ ፥ የስእል ፣ የጅምላስቴክ ወዘተን በመጠቀም ህጻናት እና ወጣቶችን በትምህርታቸው የበለጠ ከማጠንከር በተጨማሬ ተስጦዋቸውን በዚ ተቆዋም ፈልገው እንዲያገኞ ማገዝ ነው።

 

ስለ ሰለሞን ፣ ስለSunEko ፕሮጀክት ወይም አዲስ ስለከፈተው የበይነመረብ (internet) ሬዲው ከታች የተቀመጡትን ቁልፍ በመጫን ሬዲውኖንም መከታተል ፣ የሰለሞንንም አስቂኝ ፣ አዝናኝ ፣ አስተማሬ ቪዲውችን እና ምስሎችን መመልከት ይችላሉ። ፕሮጀክቶንም በሃሳብ ፣ በቁሳቁስ ፣ በገንዘብ ለመደገፍ ከፍለጎ  እሱን በቀጥታ ማነጋገር በቀላሎ ማግኝት ይችላሎ። በማህበራዊ መገናኛ ዘዲዎች ምላሹ ፈጣን ነው።   

"በሂወታችን ከልብ የምንወደውን ስራ ለመስራት መታገል አለብን፣ ለምን በምንወደው ስራ ብንጠመድ እንኮዋን ስራው ስራነቱ ቀርቶ መዝናኝችን ነው የሚሆነው። "                                                              

                 ሰለሞን ለማ ( ሶልጂት ) 

"We are our choices"

     ሰለሞን ሶልጅት ስንት የአለም ሃገራት እና ትልቅ ከተሞች ተዘዋውርዋል ?  

 ከስንት አለማቀፍ ቦድኖች ጋር ትርዒት አቅርብዋል  ?

2019: - Cirqus du Soleli 

            ካንዳአውሮፓን ቶር 

-----

2018:

          በርሊን ቲያትር Tpi - Slack Wire

          Vodafon ኩባንያ ሙኒክ - ቤተሰብ ዳ ሙንቼን።         

   

Rotary BenefizGala - Fssen

           ስቱታካሉ - ፌስቲቫል - ሙኒክ

           ቤኔክቸር - ፌስቲቫል Benediktbeuern

            „Unexpected Festival” - አርሰቶችን ማለፍ

           5 Jahre Hofstatt - የኩባንያው አመታዊ በዓል

           Semmelproduktion Afrikanische Show   - MAAG ሃሌ ዙሪክ

 

2017 ሴላኩሮባትክ በሀምቡርግ በሴሚልProduction

          Galaveranstaltung - የስፖርት ክስተት ግሬዝሪ

           ዊኒየር ካወር ፣ ደቡብ ታይሮል

           የአዲስ አበባ ኢትዮጵያ “ናhooTV” ትር showት

           በአፍሪቃ ምሽት / የወንዶች በዓል / በዓል በአፍሪካ ምሽት አስተባባሪ / ሞሉ አስተባባሪ "African Night"  Flussfestival 2017 in Wolfratshausen 

          አዲስ አበባ - FetaTVShow - ዝነኛ የመዝናኛ ውድድር - ሽልማት

2016: (ጀርመን) የ BMW የመኪና ሙዚየም ውስጥ - የእሳት ትርዒት አሳይ  

          (ጀርመን) በVW የአዲስ መኪና መመረቅያ መክፈቻ ስነስርአት አዘጋጀ  

          (ኔዘርላንድስ) Opkikker - ከAerial Art Magical Theater ቡደን ጋር ትርዒት አቀረበ  

          (ጀርመን) Marktoberdorf ውስጥ "Modeon-የስብሰባ አዳራሽ  ውስጥ ትርዒት አዘጋጀ

2015: (ጀርመን) ከPyrostyx ቦድን ጋር የLED ትርዒት አቀረበ

          (ጀርመን) ውስጥ - ከ„Vaganti - Artistic Theater“ አርቲስቲክ ቡድን ጋር ቲያትር አቀረበ

2014: (ሆንግ ኮንግ) በ„Aerial Angels“ ቡድን (ከአውስትራልያ)  "የሰማይ መላእክት" በሚል ቲያትር ላይ ተሳተፈ

          (ዱባይ) Pyrostyx እና Flyboard - በመተባበር ለዱባይ ንጉስ መሐመድ ቢን ራሺድ አል መኽቱም በቀረበ ስነስርአት ላይ ትርዒት አቀረበ

          (ኢርቢል ኮርዲስታን) ውስጥ ከ"Fantastica world Internation ጋር የገመድ ትርዒት  አቀረበ

 

2013: (ፖርቱጋል)  ከ"Circo Mundial Mariani" ቲያትር አቀረበ

2012: (ጀርመን) ከ"Adessa" ቡድን ጋር በጀርመን ውስጥ  በተለያዩ ከተምች ትርዒት አቀረበ

2011: (ላስ ቬጋስ) ውስጥ የዳንስና Quick Change ትርዒት  አቀረበ

2010 : ( ኔው ዎርክ፣ ችካጎ ፣ አትላንታ ፣ ፌላ ደልፌያ ወዘተ) ሞሉ የሰርከስ ትርኢቶን ከ አቤሲንያ ቦድኖ ጋር በመሁን አቅርብዋል።

 

2009: (ዩናይትድ ስቴትስ) ከ"Universoul ሰርከስ" ተቆዋም ጋር በ 14 ከትሞች ትርዒት አቅርብዋል

2008: (ቤልጂየም) ውስጥ "Rose- Mary Malter" የሰርከስ ትርዒት ድርጅት ጋር ትርዒት አቀርበዋል

          (ጀርመን) "Afrika Afrika" ከተባለ ድርጅት ጋር ትርዒት አቀርበዋል

2007: (አውሮፓ) ውስጥ በተለያዩ አገሮች ውስጥ ከ"Mother Afrika Zirkus" ጋር ትርዒት አቀርበዋል

2006: ( ቤጄንግ ቻይና) ውስጥ በቻይና እና አፍሪካ የትብብር መርሃ ግብር ላይ 52 የአፍረካ መርዎች በተገኙበት (FOCAC) ጋር ትርዒት አቀርበዋል

bottom of page