ሰይፉ ፋንታሁን ታሰረ – ዛሬ ሊፈረድበት
ሰይፉ ፋንታሁን በቀረበበት ሀሰተኛ ወሬ የማሰራጨት ክስ በትላንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ሰይፉ በመናገሻ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት ትላንት በቀረበበት ወቅት ‹‹አዎ ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ›› በማለት የእምነት ቃሉን እንደሰጠ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ መፈፀሙን በማመኑ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር እንዲቆይ አዟል፡፡ በዚህ መሰረት ሰይፉ ፋንታሁን በአሁኑ ወቅት በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡ በዛሬው ዕለት በሚውለው ችሎት የእስር ወይንም የገንዘብ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል፡፡
ለክስ የዳረገው ጉዳይ በቴዎድሮስ ተሾመና ቴዎድሮስ ተሾመ ድርሰቴን ሰርቆኛል ብለው ክስ በመሰረቱት ግለሰብ ዙሪያ በሬዲዮ ያሰራጨው ወሬ ነው፡፡ የሁለቱ ግለሰቦች ክስ በፍትሀብሄር እየታየ በነበረበት ሰዓት ሰይፉ በችሎት ያልተባለን ነገር ተብሏል ብሎ በማውራቱ ነው የተከሰሰው፡፡
ከዚህ ቀደም ሳያት አህመድ በዚሁ ፍርድ ቤት ሰይፉ ላይ ክስ አቅርባ እንደነበርና ጉዳዩ በሽምግልና ተድበስብሶ እንዲቀር መደረጉ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ ajebnew . com
ASK THE POPULAR
Ziggy zaga comming soon Addis Addis Radio to answer all your questions.
የዚጊ ዛጋ አድናቂዉች ዚጊን መጠየቅ የምጥፈልጉተን ጥያቄ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን የጠየቃችሁትን ጥያቄ አንጠይቀዋለን ዚጊ ዛጋ መልስ ይሰጥበታል።