top of page

"በሂወታችን ከልብ የምንወደውን ስራ ለመስራት መታገል አለብን፣ ለምን? በምንወደው ስራ ብንደክም ፡ በስራው ብዛት ብንጠመድ እንኩዋን ስራው ስራነቱ ቀርቶ መዝናኛችን ነው የሚሆነው። "  

           ሰለሞን ሶልጂት  

“ሰኒኮ አርት ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት” አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡

 

 

 ይህ ድርጅት የተቋቋመው አለም አቀፍ የሰርከስ አርቲስት በሆነው እና በአሁኑ ሰአት ዋና መቀመጫውን ጀርመን ውስጥ ባደረገው ሰለሞን ሶልጂት አማካኝነት ሲሆን ፡ ጥበብ ማህበረሰብ ውስጥ የተሻለ መልካም ለውጥ ያመጣል በሚል እሳቤ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በዋንኛነት ህጻናትን እና ወጣቶችን የሚያሳትፍ ነው፡፡ 

 

 

ይህ ፕሮጀክትም 150 ለሚጠጉ በአዳማ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ህፃናት የሰርከስ እና የተለያዩ ጥበባት ስልጠና፤ የጉብኝት ፐሮግራሞች፤ የማህበራዊ ስርከስ ፕሮግራሞች፤ የትምህርት እና ማስጠናት ስራ፤ የስነልቦና እና የምግብ አቅርቦትን ያጠቃልላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

ከ90 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንዲሁም እምቅ አቅም ያላት ኢትዮጲያ በአሁኑ ሰአት እጅግ ትልቅ ቁጥር ያላቸው ህጻናት እና ወጣቶች ይገኙባታል፡፡ እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች እንደመልካቸው ያላቸው ችሎታ እና ዝንባሌ ይለያያል ከዚህም ውስጥ የሰርከስ ፡ የጄምላስቲክ እና የተለያዩ ጥበባት ተሰጥዎ ማግኛ እና ማሳደጊያ ቦታ ማጣት አንዱ ችግር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ “ሰኒኮ አርት ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት” ለመጀመር ያሰበው ይህ ትልቅ ማእከል ከስልጠና ባለፈም ኢትዮጲያ ውስጥ ጥበብ በራሷ ማህበራዊ እድገት እና ለውጥ እንድታመጣ ያቀደ ነው፡፡ ሁሉም አይነት ጥበብ የራሱ የሆነ አለም አቀፍ ቋንቋ እንደመሆኑ መጠን ይህንንም በመጠቀም የሚታይ ማህበራዊ ለውጥን ለማምጣት ታቅዷል፡፡ 

 

“ሰኒኮ አርት ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት” አዳማ ላይ ጀምሮ በ 5 የኢትዮጵያ ከተሞች ማእከሎችን ከማስፋተም አለምን ለመድረስ ያቅዳል፡፡ እንደሁም መርሃ ግብሩን በህፃናት ጀምሮ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ለመንካት ያቅዳል፡፡እርስዎም የSunEko አንዱ የቤተሰብ አባል ይሁኑ።

 

ፕሮጀክቶንም በሃሳብ ፣ በቁሳቁስ ፣ በገንዘብ ለመደገፍ ከፍለጎም በኢሜል ወይም በሰኒኮ ኦፊሴላዊ የፋስቡክ ገጽ መልክትዎን ይላኩ፡፡

ሰለሞን እንደሚለው "አሁን የኔ ጊዜ ነው እዚ ያደረሰኝን ህዝብረተሰብ የማግዝበት ሰርከስ ናዝሬት በነበርኮበት በርካታ አመታትም እያጨበጨበ የሰርከስ ትርዒት ሳቀርብ በርታ እያለ ላጠነከረኝ ህዝብ እንዴሁም ከ 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በነጻ አስተምራ ቻይና ድረስ ልካ Professional ላረገችኝ ሃገሬ ብድሬን የምመልስበት ውቅት ነው።"  ለዜህም ይመስላል በህገር አቀፍ ደረጃ 5 የጥበብ ማእከላት ለመክፈት በአዳማ ከተማ አንድ ብሎ የጀመረው። መቀመጫው አዲስ አበባ የሚሆነው ይህ ተቆዋም SunEko ይባላል ይህም በመጀመርያው መርሃ ግብር ለ150 ህጻናት እና ወጣቶችን የሚያቅፍ ይሆናል የዚህ ተቃም አላማም የተለያዮ የሰርከስ ፣ የሞዚቃ ፥ የስእል ፣ የጅምላስቴክ ወዘተን በመጠቀም ህጻናት እና ወጣቶችን በትምህርታቸው የበለጠ ከማጠንከር በተጨማሬ ተስጦዋቸውን በዚ ተቆዋም ፈልገው እንዲያገኞ ማገዝ ነው።

 

ስለ ሰለሞን ፣ ስለSunEko ፕሮጀክት ወይም አዲስ ስለከፈተው የበይነመረብ (internet) ሬዲው ከታች የተቀመጡትን ቁልፍ በመጫን ሬዲውኖንም መከታተል ፣ የሰለሞንንም አስቂኝ ፣ አዝናኝ ፣ አስተማሬ ቪዲውችን እና ምስሎችን መመልከት ይችላሉ። ፕሮጀክቶንም በሃሳብ ፣ በቁሳቁስ ፣ በገንዘብ ለመደገፍ ከፍለጎ  እሱን በቀጥታ ማነጋገር በቀላሎ ማግኝት ይችላሎ። በማህበራዊ መገናኛ ዘዲዎች ምላሹ ፈጣን ነው።   

bottom of page